አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦማን ሱልጣኔት የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሐመድ ያሲን ከሰላላህ ነጻ የኢኮኖሚ ዞን ሀላፊዎች ጋር ተወያዩ።
አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሐመድ ያሲን እና የኤምባሲው ሰራተኞች ከሰላላህ ነጻ የሚኮኖሚ ዞን ስራ አስፈጻሚ ከአቶ አሊ ሞሀመድ ታቡክ ጋር በተለያዩ የንግድና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ ስላሉ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የሰላላ ነጻ የኢኮኖሚ ዞን ኃላፊዎችም በበኩላቸው÷ ስለ ነጻ የኢኮኖሚ ዞኑ አሰራርና በዉስጡ ስላሉ አገልግሎቶችና ፋብሪካዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
በተደረገዉ ዉይይት በኢትዮጵያና በኦማን መካከል ያለዉን የኢኮኖሚ ግንኙነት ለማጠናከር በትብብር ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የኤምባሲዉ የልዑክ ቡድን በዞኑ ዉስጥ ያሉ የተለያዩ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን መመልከቱን በበኦማን ሱልጣኔት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!