አዲስ አበባ ፣ ጥር 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካውያን የታሪክ ተናጋሪዎች ታሪካቸውን በራሳቸው ቋንቋ በድምፅ በመቅረጽ የሚያስተዋውቁበት መተግበሪያ ተሰራ።
አማርኛን ጨምሮ በሌሎች ቋንቋዎች የአፍሪካን ታሪኮች ወደ ድምፅ መጽሐፍት መቀየር የሚያስችል መተግበሪያ በጋናው የሶፍት ዌር ኩባንያ ሶፍትትራይብ ባለቤት ሄርማን ቺነሪይ-ሄስ ተሠርቷል።
የአፍሪካውያን ድምፆች (Afrikan Echoes) የተሰኘው መተግበሪያ በመጪው መጋቢት ወር ያልተነገሩ 50 የአፍሪካውያን ነባር ታሪኮች በዩሩባ ይፋ ያደርል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሲ.ኤን.ኤን ዘግቧል።
ኩባንያው አማርኛ እና ስዋሂሊ ቋንቋዎችን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ቋንቋዎች ታሪኮችን ተርጉሞ ይፋ ያደርጋል ተብሏል።
በዚህም አፍሪካውያን ታሪኮቻቸውን በራሳቸው ቋንቋ በድምፅ በመቅረጽ ለኩባንያው ይልካሉ።
ድምፆቹም ወደ መተግበሪያው ከመካተታቸው በፊት በባለሞያዎች ቡድን ይገመገማሉ።
የሚላኩ የአፍሪካውያን ታሪኮች ግን አወዛጋቢ እና የማያግባቡ፤ ልዩነትን የሚያሰፉ እንዳይሆኑ እንደ ተግዳሮት ተቀምጧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!