የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓታት 437 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 549 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

By Meseret Awoke

January 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 342 የላቦራቶሪ ምርመራ 437 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት 549 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 4 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

እስካሁን በወረርሽኙ ምክንያት 2 ሺህ 75 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 11 ሺህ 744 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 219 ሰዎች ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡

ወረርሽኙ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 930 ሺህ 478 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡

ከእነዚህም መካከልም 134 ሺህ 569 በወረርሽኙ የተያዙ ሲሆን አሁን ላይ 11 ሺህ 744 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!