ቢዝነስ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የምርት መቀበያ መጋዘን ግንባታ በቴፒ ገንብቶ ማጠናቀቁን ገለጸ

By Abrham Fekede

January 25, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ደረጃውን የጠበቀ የምርት መቀበያ መጋዘን ግንባታ በቴፒ ገንብቶ ማጠናቀቁን የገለጸ ሲሆን በኤሌክትሮኒክ ግብይትና ጨረታ 698 ተገበያዮችን ማሰልጠኑንም አስታወቀ፡፡

ምርት ገበያው ይህንን ያስታወቀው የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው መንፈቅ የስራ ዕቅድ አፈጻፀም ላይ ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡

ምርት ገበያው ከመደበኛ ዕቅድ በተጨማሪ በለውጥ ስራዎች የአሰራር ስርዓቱን ለማሻሻል ለደንበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት የሚረዱ የተለያዩ ማሻሻያዎች መከናወናቸው ገልጿል፡፡

በተጨማሪም በዚህ ዓመት ሁለት አዳዲስ ባንኮችን ወደ ግብይት ስርዓቱ በማስገባት የክፍያ ስርዓቱን ለተገልጋዮች የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ መቻሉንም ነው ያስታወቀው፡፡

የቅድመ-ግብይት መረጃ ለጥራጥሬና ቅባት እህሎች ተግባራዊ መደረጉ፣ የደረጃ አወጣጥ ስራን ዲጂታላይዝ በማድረግ በእያንዳንዱ ባለሙያ የሚሠጡ ደረጃዎችን ለማወቅና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ የሚያስችል አሰራር ስርዓት ተግባራዊ መደረጉ ተጠቅሷል፡፡

እንዲሁም በግማሽ ዓመት ዥንጉርጉር ቦሎቄና የርግብ አተር ምርቶች ወደ ግብይት ስርዓቱ መግባታቸው ተገልጿል፡፡

የምርት ገበያው ወደ ዘመናዊ የግብይት ሊያስገባቸው የሚገቡ ምርቶችን በመለየት የክልል የቅርንጫፍ ማስፋፋትን በተመለከተ በየትኞቹ የክልል ከተሞች ተጨማሪ ቅርንጫፎችና የግብይት ማዕከላት ሊገነቡ እንደሚገባ ተወያይተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!