ቴክ

በውሃ ላይ የሚሰራ የኤሌክትሪክ ብስክሌት በገበያ ላይ ዋለ

By Tibebu Kebede

January 08, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍቢሲ) በውሃ ላይ የሚሰራ የኤሌክትሪክ ብስክሌት በገበያ ላይ መዋሉ ተነገረ።

ማንታ 5 የተባለው የኒውዝላንድ ኩባንያ ኤክስ ኢ 1 የተሰኘችውን እና በውሃ ላይ የምትሰራውን የኤሌክትሪክ ብስክሌት በላስ ቬጋስ አስተዋውቋል።

ብስክሌቱ በፔዳል የሚሰራ ሲሆን፥ አንድ ጊዜ ባትሪ ከተሞላ በኋላ ለአንድ ሰዓት ያክል መጠቀም ይቻላል።

በሰዓትም እስከ 20 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር ድረስ መጓዝ ይችላልም ነው የተባለው።

አዲሱ ብስክሌት የ6 ሺህ ፓውንድ ዋጋ ተቆርጦለታል።

ብስክሌቱን ለዕይታ ለማብቃት እስከ 10 አመት ጊዜ እንደፈጀ ኩባንያው ምርቱን ባስተዋወቀበት ወቅት ገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ