የሀገር ውስጥ ዜና

የፌደራል ስርዓት እንዲጎለብት የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ

By Tibebu Kebede

January 23, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ስርዓት እንዲጎለብት የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ ገልጸዋል።

ምክር ቤቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በፌደራል ስርዓቱ ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት እያደረገ ነው።

የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ለፌደራል ስርዓቱ መጎልበት ከፍተኛ ሚና እንዳለው በውይይቱ ተገልጿል፡፡

ህገመንግስቱ ለሁሉም ዜጎች አንድ የፖለቲካ ተሳትፎን የሚያረጋግጥ ቢሆንም እስካሁን በምክር ቤቶች እና በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑን ጥናቶች ያመላክታሉ።

የሁሉንም ዜጎች እኩል የፖለቲካ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስልጣንና ተግባር ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በተለይም የሴቶችን የዴሞክራሲ ባህል ማሳደግ ለፌደራል ስርዓቱ ከፍተኛ ሚና አለው ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!