ስፓርት

የሴኔጋልና የሊቨርፑሉ አጥቂ ሳዲዮ ማኔ የአፍሪካ የዓመቱ ኮኮብ ተጫዋች ሆነ

By Tibebu Kebede

January 08, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን እና የሊቨርፑሉ አጥቂ ሳዲዮ ማኔ በአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) የአፍሪካ የዓመቱ ኮኮብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ፡፡

ሳዲዮ ማኔ የዓመቱ ኮኮብ ተጫዋችነት ሽልማትን ያገኘነው የቡድን አጋሩን ሞሃመድ ሳላህ እና የአልጀሪያና የማንቼስተር ሲቲውን የመስመር ተጫዋች ሪያድ ማህሬዝን አስከትሎ ነው።

የ27 ዓመቱ የሊቨርፑል አጥቂ በ2018/2019 በሁሉም ውድድሮች 30 ጎሎችኝ በማስቆጠር ቀያዮች የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን እንዲያነሱ አስችሏል፡፡

እንዲሁም ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን በ13 ነጥብ ልዩነት እየመራ በሚገኝበት የዘንድሮው የውድድር ዘመን ሴኔጋላዊው ኮኮብ 15 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡

ማኔ ሽልማቱን በተቀበለበት ወቅት ይህን ሽልማት በማሸነፌ ደስታ እና ኩራት ተሰምቶኛል፤ እግር ኳስ ስራየ ነው እወደዋለሁም ብሏል፡፡

የሽልማት ስነ ስርዓቱ በግብፅ ሁራግሃዳ የተካሄደ ሲሆን፥ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ሽልማት ማግኘት የቻሉት ሞሃመድ ሳላህም ሆነ ሪያድ ማህሬዝ በስነ ስርዓቱ ላይ አልተገኙም፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ