ዓለምአቀፋዊ ዜና

170 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ኢራን ውስጥ ተከሰከሰ

By Tibebu Kebede

January 08, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29 ፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ንብረትነቱ የዩክሬን አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 737 አውሮፕላን 170 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ ኢራን ውስጥ ተከስክሷል።

አውሮፕላኑ ከኢራን ዋና ከተማ ቴህራን አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ዩክሬቭ መዲና ኬቭ መብረር ከጀመረ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መከስከሱን የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በአደጋው በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ መንገደኞች እና የበረራ ሰራተኞችን ጨምሮ 180 የሚደርሱ ሰዎች በሙሉ ህይወታቸው ሳያልፍ እንዳልቀረ ተነግሯል።

የዩክሬን መንግስትም አደጋውን የሚያጣራ ቡድን እንደሚቋቋም ገልጿል።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ አደጋውን ተከትሎ በኦማን የነበራቸውን ጉብኝት መሰረዛቸው ተገልጿል።

የአደጋው መንስኤ በቴክኒክ ችግር አልያም ኢራንና አሜሪካ ከገቡበት ግጭት ጋር የተየያዘ ስለመሆኑ አለመሆኑ አልታወቀም።

ምንጭ ፦ ቢቢሲ