ዓለምአቀፋዊ ዜና

ኢራን በኢራቅ በሚገኝ የአሜሪካ የዓየር ሀይል ሰፈር ላይ የሚሳኤል ጥቃት ፈፀመች

By Tibebu Kebede

January 08, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢራን በኢራቅ በሚገኝ የአሜሪካ ዓየር ሀይል የጦር ሰፈር ላይ የባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ፈፀመች።

የአሜሪካ የመከላከያ መስሪያ ቤት ፔንታጎን ሁለት የጦር ሰፈሮች ጥቃት እንደተፈፀመባቸው አስታውቋል።

የኢራን የመንግስት ቴሌቪዥን ጣቢያ የባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃቱ የተፈፀመው ባለፈው ሳምንት የሀገሪቱ ግንባር ቀደም ወታደራዊ መሪ የሆኑት ቃሲም ሶሊማኒ በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትእዛዝ ለመገደላቸው የተሰጠ አፀፋ መሆኑን ዘግቧል።

በአካባቢው የሚገኙ የትኛውም የአሜሪካ ወዳጅ የሆነ እና የዋሽንግተንን ወታደሮች እያስተናገደ የሚገኝ ሀገር ሁሉ ኢላማ መሆኑንም ቴሂራን አስጠንቅቃለች።

በጥቃቱ ምን ዓይነት ጉዳት እንደደረሰ እስካሁን ግልፅ የተደረገ ነገር የለም።

ዋይት ሀውስ በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የተሰጣቸው ሲሆን፥ በሁኔታው ላይ ከብሄራዊ የደህንነት ቡድናቸው ጋር እየመከሩ መሆኑን ነው ያስታወቀው።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ