Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጊኒ ኮናክሪ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ጊኒ ኮናክሪ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጊኒ ኮናክሪ ሲደርሱም የጊኒ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አልፋ ኮንዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጊኒ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግን ዓላማ ያደረገ መሆኑ ነው የተመለከተው።

ነገ ሁለቱ መሪዎች በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የጊኒ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አልፋ ኮንዴ ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት ሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂክ አጋርነትን የሚያጠናክሩ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን መመስረቻ ስምምነት ያደረጉ ሲሆን፥ በትምህርት፣ ጤና፣ በገንዘብና ማኔጅመንት፣ በግብርና እንዲሁም በባህልና ቱሪዝም መስኮች ለመተባበር የሚያስችል ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

 

በአልአዛር ታደለ

Exit mobile version