አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በ178 ሚሊየን ብር የተገነባው የኮምቦልቻ አጠቃላይ ሆስፒታል ተመርቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።
ሆስፒታሉ ለአካባቢውን ህብረተሰብ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
የሆስፒታሉ ግንባታ ለ10 ዓመታት ተጓቶ እንደነበር እና በሕዝቡ ዘንድ ቅሬታ ፈጥሮ እንደነበርም ነው የተገለጸው።
በደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር የሚያወጡ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ከትናንት ጀምሮ መመረቃቸውን ከአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!