አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ቱርክ በመካከላቸው ያለውን የንግድ ልውውጥ 1 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በተገኙበት የኢትዮ ቱርክ ስምንተኛው የኢኮኖሚ፣ ንግድ እና የቴክኒካል ትብብር ኮሚሽን ስብሰባ በአንካራ ተካሂዷል።
በዚህ ወቅት ሀገራቱ በመካከላቸው ያለውን የንግድ ልውውጥ ለማሻሻል ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
እንዲሁም የንግድ ጉድለትን ፣ የንግድ እንቅፋቶችን ለመቀነስ ፣ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ እና አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችን ለመደገፍ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተጠቁሟል።
እንደ ቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ በፈረንጆቹ 2019 የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ 398 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ደርሷል።
ከዚህ ውስጥ ቱርክ ወደ ኢትዮጵያ የምትልከው የምርት መጠን 378 ነጥብ 3 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መሆኑ ተገልጿል።
ከዚህ ውስጥ ቱርክ ወደ ኢትዮጵያ የምትልከው የምርት መጠን 378 ነጥብ 3 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መሆኑ ተገልጿል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!