የሀገር ውስጥ ዜና

በርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ የሚመራ ልዑክ በደቡብ ወሎ ዞን የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎበኘ

By Tibebu Kebede

January 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር የሚመራ የከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በደቡብ ወሎ ዞን የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎበኘ ።

በዚህ ወቅትም በቃሉ ወረዳ ገርባ ከተማ የተገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል።

ትምህርት ቤቱ 15 መማሪያ ክፍሎች ያሉትና ባለ 2 ወለል ህንጻ ሲሆን ቤተ ሙከራና ቤተ መጽሐፍትም አሉት፡፡

ትምህርት ቤቱ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን ከ7 ሚሊየን ብር በላይ የሸፈነው የአካባቢው ህብረተሰብ  መሆኑን አብመድ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!