አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) ነገ በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ይከበራል።
በዓሉ በተለያዩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ስነ ስርዓቶች ተከብሮ ይውላል።
በተለይም በዓሉ በቅዱስ ላልይበላ ከተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የመጡ እንግዶች፣ የውጭ ሃገር ጎብኝዎችና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በድምቀት ይከበራል።
የሃይማኖት መሪዎች በዓሉን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን በመተሳሰብ፣ በአንድነትና በፍቅር እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።
አቅመ ደካሞችን በማገዝ በዓሉን ማክበር ይገባል ያሉት የሃይማኖት መሪዎቹ፥ በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሆን ዘንድም ተመኝተዋል።