ቢዝነስ

ኢንተርፕራይዙ በስድስት ወራት ከ193 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

By Tibebu Kebede

January 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከ193 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ከዚህ ባለፈም ከልዩ ልዩ ገቢዎች 12 ሚሊየን 640 ሺህ 310 ብር የሰበሰበ ሲሆን፥ በአጠቃላይ 193 ሚሊየን 385 ሺህ 165 መሰብሰብ ችሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ በአዲስ- አዳማ እና በድሬዳዋ- ደወሌ የክፍያ መንገዶች 4 ሚሊየን 811 ሺህ 698፥ የትራፊክ ፍሰት ለማስተናገድ አቅዶ 4 ሚሊየን 413 ሺህ 682 የትራፊክ ፍሰት ማስተናገዱንም አስታውቋል፡፡

ይህም የእቅዱን 92 በመቶ መሆኑንም ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከክፍያ መንገድ አገልግሎት 194 ሚሊየን 483 ሺህ 127 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 180 ሚሊየን 744 ሺህ 855 ብር መሰብሰቡንም ነው ያስታወቀው፡፡

ኢንተርፕራይዙ የመንገዶቹን ደህንነት ከማስጠበቅና የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ ከሚሰራው ስራ ባሻገር፥ በመንዶቹ ብዙ ምልልስ ያደረጉ፣ የትራፊክ አደጋ ያላደረሱ፣ በስነ ምግባራቸው ምስጉን የሆኑ አሽከርካሪዎችን በመለየት ‹‹ኤክስፕረስ ማይልስ›› በሚል የመጀመሪያውን ዙር የደህንነት አምባሳደሮች ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም የጥገና አቅምን በማሳደግ በውስጥ አቅም 5 ነጥብ 1 ኪሌ ሜትር የመንገድ አካፋይ ብረት እንዲሁም 0 ነጥብ 93 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የአጥር ጥገና በአዲስ- አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ አከናውኗል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!