አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁዋዌ መንግስት የቴሌኮም ዘርፉን መክፈቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ በሰፊው ለመንቀሳቀስ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
ኢትዮጵያ እያደገች እና ለወደፊት በእጅጉ አስፈላጊ እየሆነች መምጣቷን ከሰሃራ በታች በሚገኙ 22 ሀገራት የሁዋዌ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሎይሴ ታማልጎ ተናግረዋል።
የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው የኩባንያው ስትራቴጂ በጣም ቀላል ነው ብለዋል።
ሁዋዌ ኩባንያ መንግስት የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ለግል ዘርፉ ሲያስተላልፍ ቦታ ለማግኘት ማቀዱንም ሃላፊው አስታውቀዋል።
ቢዝነስ ላይቭ በዘገባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ የግሉ ዘርፍ እንዲሳተፍባቸው እቅድ ከያዙባቸው ተቋማት መካከል የቴሌኮም ዘርፉ አንዱ መሆኑን አስታወሷል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!