Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በማዕከላዊ ቻይና መንስኤው ያልታወቀ የሳምባ ምች በሽታ ተከስቷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በማዕከላዊ ቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ መንስኤው ያልታወቀ ተላላፊ የሳንባ ምች በሽታ መከሰቱ ተሰምቷል።

የአካባቢው የጤና ባለሙያዎች እንዳስታወቁት በተከሰተው ተላላፊ የሳምባ ምች በሽታ እስካሁን የተያዙ ሰዎች ቁጥር 59 ደርሷል።

በበሽታው የተጠቁ ሰዎችም በገለልተኛ ጤና ጣቢያ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ነው የተገለጸው።

ከተጠቂዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸው 163 ሰዎችም በተለየ ስፍራ ተቀምጠው በህክምና ባለሙያዎች ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ተጠቅሷል ።

በበሽታው ከተያዙት ውስጥ 11 የሚሆኑት ሰዎች በፅኑ ታመው የነበረ ሲሆን፥ በተደረገላቸው ህክምና አሁን ላይ አራቱ ታማሚዎች ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተመላክቷል።

የበሽታንውን መንስኤ ለማወቅም ባለሙያዎች ምርምር እያካሄዱ መሆኑን የከተማዋ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

ምንጭ፦ ሺንዋ

 

Exit mobile version