የሀገር ውስጥ ዜና

ለሃጅ እና ኡምራ ተጓዦች ቅድመ ሁኔታዎችን ማመቻቸት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

By Tibebu Kebede

January 06, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ ለዘንድሮው የሃጅ እና ኡምራ ተጓዦች ቅድመ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ እና የሳዑዲ ዓረቢያ የሃጅ እና ኡምራ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ዶክተር ሁሴን ቢን ናስር አል ሸሪፍ ተፈራርመውታል።

ስምምነቱ ለ1 ሺህ 441ኛው የሃጅ እና ኡምራ ለሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ቅድመ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያውያን ተጓዦች በቆይታቸው የተሟላ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

ምንጭ፦ spa.gov.sa/