አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በካሜሮን አዘጋጅነት የሚካሄደው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የሚመሩ ዳኞችን የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ኮሚቴ ከ31 ሀገራት 47 ዋና ዳኞች ፣ ረዳት ዳኞች እና የቪዲዮ ረዳት ዳኞችን መርጧል።
በዚህም ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ የቻን የአፍሪካ ዋንጫ በዋና ዳኝነት የምትመራ ብቸኛዋ ሴት መሆኗን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
በተመሳሳይ ሌላኛው ዓለም አቀፍ ዳኛ በአምላክ ተሰማ በቫር ዳኝነት የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ከሚመሩ ዳኞች መካከል አንዱ ሆኖ ተመርጧል።
የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ከጥር 8 ቀን 2013 እስከ ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በካሜሮን አዘጋጅነት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
በምድብ አንድ ካሜሮን፣ ማሊ፣ቡሪኪና ፋሶ እና ዚምባቡዌ ሲደለደሉ በምድብ ሁለት ሊቢያ ፣ዲሚክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ኮንጎ እና ኒጀር ተደልድለዋል፡፡
እንዲሁም በምድብ ሶስት ሞሮኮ፣ ሩዋንዳ፣ ኡጋንዳ እና ቶጎ ተገናኝተዋል።
በምድብ አራት ደግሞ ዛምቢያ፣ጊኒ፣ናሚቢያ እና ታንዛኒያ መደልደላቸው ታውቋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!