ስፓርት

3ኛው ዙር የከተማ አቀፍ የሰላም ንቅናቄ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በቦሌ ክፍለ ከተማ ተካሄደ

By Tibebu Kebede

January 10, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው ዙር የከተማ አቀፍ የሰላም ንቅናቄ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት በቦሌ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴው አምቼ መነሻውን አድርጎ ወደ ቦሌ በሚወስደው የቀለበት መንገድ ላይ ተካሂዷል።

ሶስተኛው ዙር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ “ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ ፤ ለመከላከያ ሰራዊት ቅድሚያ እሰጣለሁ!” በሚል መሪ ሀሳብ መካሄዱን ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሸን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እራሱን ችሎ ተቋማዊ አድርጎ ለማስቀጠል ከተማ አስተዳደሩና አዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ያስጀመረው ይህ የሰላም ንቅናቄ ዛሬ ላይ ሶስተኛ ዙር ማህበረሰብ አቀፍ ላይ ደርሷል ብለዋል።

ሁላችንም በየዙሩ ያገኘናቸውን የሰላም ፣ የአንድነት ፣ የፍቅር እና የወንድማማችነት ተምሳሌት በየደረጃው በቀጣይነት ማረጋገጥ ይኖርብናል ነው ያሉት።

በዛሬው ሁነት ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፥ የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የቀጣይ አራተኛው ዙር የአካል ብቃት እንቅሰቃሴ አስተናጋጅ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ነው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!