ስፓርት

ጅማ ለፕሪሚየር ሊጉ ውድድር መሰናዶ አስፈላጊ ዝግጅት ማድረጓን የከተማዋ ከንቲባው አረጋገጡ

By Tibebu Kebede

January 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ ምዕራፍ ጅማ ላይ ይካሄዳል።

ይህን ተከትሎም ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆኑን የከተማው ከንቲባ በላኩት ደብዳቤ ማረጋገጣቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ጅማ ከተማ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ከሰባተኛው እስከ 11ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎችን ታዘጋጃለች።

ይህን ተከትሎ በቅርቡ ወደ ሥፍራው ያቀናው የሊግ ኩባንያው የልዑክ ቡድን አብዛኛው ከሆቴል አቅርቦት፣ የልምምድ ሜዳ፣ የፀጥታ እና ከኮቪድ ምርመራ ማዕከል ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የተሟሉ እንደሆኑ ጨዋታዎቹ የሚደረጉበት የጅማ ዩኒቨርሲቲ መጫወቻ ሜዳ በተወሰነ መልኩ በቀሩት ቀናት ማስተካከያ እንዲደረግበት ምክረ ሀሳብ ሰጥቶ እንደተመለሰ ዘገባው አስታውሷል።

ይህን ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የመጫወቻው ሜዳ የማስተካከያ ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሆነ እና በቀሩት ጥቂት ቀናት ሙሉ ለሙሉ ለጨዋታ ዝግጁ እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

የከተማዋ ከንቲባ አቶ ቲጃኒ በበኩላቸው ጅማ ከተማ ይህን ትልቅ ውድድር እንግዶቿን ተቀብላ ውድድሩን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ለሊግ ኩባንያው በላኩት የማረጋገጫ ደብዳቤ አስታውቀዋል።

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!