የሀገር ውስጥ ዜና

በቦረና ዞን ድሬ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Tibebu Kebede

January 05, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ድሬ ወረዳ በዛሬው ዕለት በደረሰ የመኪና አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

አደጋው የደረሰው ወደ ዲሎ ገበያ ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመገልበጡ ነው፡፡