Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሲቪል፣ የፖለቲካ እና ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መብት ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲቪል፣ የፖለቲካ እና ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መብት ላይ ውይይት ማካሄዱን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡

ውይይቱ በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው የሶስተኛውን ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃ ግብር ረቂቅ ሰነድ ላይ ነው ተብሏል፡፡

በውይይቱ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት እና ከሃይማኖት ተቋማት የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በውይይቱ ላይ ከዚህ በፊት ሁለት የሰብዓዊ መብት ብሄራዊ የድርጊት መርሀ ግብር ሰነዶች ተዘጋጅተው ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

የሶስተኛው የብሄራዊ የድርጊት መርሃ ግብር በይበልጥ ተፈፃሚ ለማድረግ ያለፉት ሂደቶች በሚገባ መዳሰሳቸውንም አስረድተዋል፡፡

ሰነዱ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አንገብጋቢ ጉዳዮችን ያካተተና ለአፈጻፀምና ለአተገባበር በሚመች መልኩ መዘጋጀቱን ከተለያዩ ወገኖች ግብዓት መሰብሰቡን አስታውሰዋል፡፡

በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የብሄራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃ ግብር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሪት መድሃኒት ታመነ የመርሃ ግብሩ በሀገሪቱ የሰብዓዊ ግንዛቤ እንዲጎለብትና የሰብዓዊ መብት ጥበቃ በተደራጀ፣ በተቀናጀና ቀጣይነት ባለው መልኩ የበለጠ እንዲሻሻል ያለመ መሆኑን ነው  ያብራሩት፡፡

በሰነዱ የተካተቱ ዋና ዋና ተግባራትና አጠቃላይ በረቂቅ ሰነዱ ዙሪያ ውይይት በማድረግ ግብዓት እንደተሰበሰበ መጠቀሱን

ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

Exit mobile version