Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአማራና በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራና በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፡፡
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ.ም በክልሉ የተሰጠው የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን የየክልሎቹ ትምህርት ቢሮዎች አስታውቀዋል፡፡
በአማራ ክልል ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 96 ነጥብ 85 በመቶ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል መዘዋወራቸው ታውቋል፡፡
ይህን ተከትሎም ቢሮው በዚህ አመት የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት በመሆኑ ለተማሪዎቹ ወላጆች እና ለትምህርት ባለድርሻ አካላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
ተማሪዎችም በየትምህርት ቤታቸው ውጤታቸውን በማየት የ9ኛ ክፍል ምዝገባ ከታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንዲያካሂዱ ቢሮው አሳስቧል፡፡
በተያያዘ ዜና በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ የሆነ ሲሆን ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 93 በመቶዎቹ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ተዘዋውረዋል፡፡
በክልሉ በአጠቃላይ 446 ሺህ 907 ተማሪዎች ፈተና የተቀመጡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 417 ሺህ 411 ወይም 93 ነጥብ 4 በመቶ ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡
ቢሮው ከአንድ ሳምንት በኋላ የ9ኛ ክፍል ትምህርት በኦሮሚያ ክልል ይጀመራልም ብሏል፡፡
ከአጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 29 ሺህ 96 ተማሪዎች ወይም 6 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑት ወደ ቀጣይ ክፍል አለመዘዋወራቸው ተገልጿል።
መረጃው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ እና የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version