ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሳዑዲ ዓረቢያ የየብስና የባሕር ድንበሯን ለኳታር ክፍት እንደምታደርግ ኩዌት አስታወቀች

By Tibebu Kebede

January 05, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳዑዲ ዓረቢያ የየብስና የባሕር ድንበሯን ለኳታር ክፍት እንደምታደርግ ኩዌት አስታወቀች፡፡

የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ናስር አል ሳባህ ሳዑዲ በቅርቡ ድንበሯን ለኳታር ትከፍታለች ብለዋል፡፡

ሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት ኢሚሬትስ፣ ኩዌት እና ግብጽ፥ ኳታር ሽብርተኞችን በመደገፍና መረጋጋት እንዳይኖር ለተቃዋሚዎች ድጋፍ ታደርጋለች በሚል ሶስት አመት ተኩል ማዕቀብ ጥለውባት ቆይተዋል፡፡

ማዕቀቡ ከዶሃ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጥን አላማ ያደረገ ሲሆን፥ በዚህ ሳቢያ ኳታር ፈታኝ ጊዜ አሳልፋለች፡፡

ሃገራቱ ማዕቀቡን ከጣሉ በኋላ ኳታር ዳግም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ለመጀመርና በወዳጅነት ለመዝለቅ 13 ቅድመ ሁኔታዎችን ታሟላ ዘንድ ማስቀመጣቸውም የሚታወስ ነው፡፡

ከዚያን ጊዜ ወዲህም ከኳታርም ሆነ ማዕቀቡን ከጣሉ ሃገራት በኩል መለሳለስ ባለመታየቱ ግንኙነታቸው ተቋርጦ ቆይቶም ነበር፡፡

ለኳታራውያን መልካም የተባለው ዜናም የባህረ ሰላጤው ሃገራት የትብብር መድረክ ጉባኤ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ ተሰምቷል፡፡

አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣንም በኩዌት የተሰማው ዜና እውነት መሆኑን ጠቅሰው ማዕቀቡን መቋጫ የስምምነት ሰነድ ይፈረማልም ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳ የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!