Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለፉት 6 ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ340 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 6 ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ340 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት 6 ወራት በ2013 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ትግባራት ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልሎችና ከህዝብ ተወካዮች የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ኮሚቴ አባላት ጋር ገምግሟል፡፡

የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ እንደተናገሩት ባለፉት 6 ወራት ከ340 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡

ገቢው የተገኘው ከ4 ሺህ 112 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ፣26 ነጥብ 9 ቶን ታንታለም፣1 ሺህ 625 ኪሎግራም ጥሬ ኦፓል፣ 37 ነጥብ 8 ኪሎ ግራም እሴት የተጨመረበት ኦፓል እና 2 ሺህ 123 ኪሎ ግራም ሌሎች የጌጣጌጥ ማዕድናት ለውጭ ገበያ በማቅረብ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለሀገር ውስጥ ገበያ ከቀረቡ የኢንዱስትሪና የኮንስትራክሽን ማዕድናት 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ ያስታወቁት፡፡

በዘርፉ ለ48 ሺህ 785 ዜጎች የስራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልሎችና ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የቀጣይ ስድስት ወራት የዕቅድ አቅጣጫዎች ተቀምጧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳ

የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version