የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ባለሃብቶች ቀን በባህር ዳር ከተማ በውይይት ተከበረ

By Tibebu Kebede

January 04, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ባለሃብቶች ቀን በባህር ዳር ከተማ በውይይት ተከበረ።

በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ በአራቱ በግብርና ንዑስ ዘርፎች በሰብል ልማት፣ በእንስሳት ሃብት ልማት፣ በወተት ላም እርባታ እና በግብርና ማቀነባበር የተሰማሩ ባላሃብቶች ተሳትፈዋል።

ውይይቱ በክልሉ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ሰፊ እና ዘላቂ የስራ እድል ለመፍጠር ያለመ መሆኑን የክልሉ የኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል።

የክልሉን የኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማሳደግ በግብርና ኢኮኖሚው የሚስተዋሉ ችግሮችን ከባላሃብቱ ጋር በቅንጅት መፍታት አስፈላጊ መሆኑን ሃላፊው ገልጸዋል።

ዘላቂ የስራ እድል ለመፍጠር እና ምርታማነትን ለማሳደግም በግብርናው ዘርፍ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ እና የማሌዥያን ተሞክሮ መውሰድ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በናትናኤል ጥጋቡ