አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በባርሴሎና የዓለም ክብረወሰንን ለማሻሻል ትሮጣለች።
የዓለም 1 ሺህ 500 ሜትር ክብረወሰን ባለቤቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ነገ በባርሴሎና በሚካሄደው የ5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር የዓለም ክብረወሰንን ለማሻሻል እንደምትሮጥ ታውቋል።
ገንዘቤ በ5 ሺህ ሜትር የሲፈን ሀሰንን 14 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ ፥ ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ ደግሞ በ10 ሺህ ሜትር የጆሰሊን ጄፕኮስጌን 29 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ ለማሻሻል ይሮጣሉ።
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ከሶስት ሳምንት በፊት በቫሌንሲያ የተካሄደውን የግማሽ ማራቶን ውድድር ማሸነፏ አይዘነጋም።
አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ17 ማይክሮ ሰከንድ ጊዜ ወስዶባት ነበር፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!