Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ብሪታንያ አስትራዜኒካ የተሰኘው የኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪታንያ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች የበለጸገውን አስትራዜኒካ የተሰኘው የኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች፡፡

በሀገሪቷ ባሉ የመድሐኒት ተቆጣጣሪዎች ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ ፍቱንና ፈዋሽ መሆኑ መረጋገጡ ነው የተሰማው፡፡

አስትራዜኒካ በብሪታንያ ፍቃድ ሲያገኝ ከፋይዘርና ከባዮንቴክ በመቀጠል ሁለተኛው ነው ተብሏል፡፡

እንዲሁም ከሌሎቹ ክትባቶች አንጻር ሲታይ በመደበኛ ማቀዝቀዣዎች ውስጥ ማስቀመጥ እንደሚቻል የተጠቀሰ ሲሆን ይህም ለአጠቃቀም እና ለአያያዝ ምቹ ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

ብሪታንያም 50 ሚሊየን ዜጎቿን መከተብ የሚያስችል 100 ሚሊየን መጠን የያዘ ክትባት ማዘዟን ገልጻለች፡፡

የዛሬ ዓመት ጥር አካባቢ ማበልጸግ የተጀመረው ይህ ክትባት ሚያዝያ ላይ በበጎፍቃደኞች ከተሞከረ በኋላ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ክሊኒካል ሙከራ መካሄዱ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version