አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ በመቐለ የሚገኘውን የፓርቲውን ዋና ጽህፈት ቤት በይፋ ሥራ አስጀመረ።
በትግራይ ክልል ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት የሚንቀሳቀሱበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩም ተገልጿል።
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል የጽህፈት ቤቱን ሥራ ማስጀመር አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በህወሓት ቡድን አምባገነንነት የፖለቲካ ፓርቲዎች በትግራይ ክልል ቢሮ ከፍተው መስራት የማይችሉበት ሁኔታ እንደነበር አስታውሰዋል።
ቡድኑ ተወግዶ በትግራይ ክልል ለውጥ በመምጣቱ ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ሌሎች ህጋዊ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት የሚንቀሳቀሱበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸዋል።
በዚህም ብልፅግና ቢሮውን በመቐለ ከፍቶ በይፋ ሥራ መጀመሩን ገልጸው፥ “ሌሎች ህጋዊ ፓርቲዎችም በተመሳሳይ መንቀሳቀስ የሚችሉበት እድል ተፈጥሯል” ብለዋል።
በትግራይ ክልል የተጀመረው የለውጥ ምዕራፍ ህዝቡን የሚያሳትፍና ወጣቱን በግንባር ቀደምትነት የለወጡ አራማጅ የሚያደርግ መሆኑንም ተናግረዋል።
ለውጡ በትግራይ ክልል ከዚህ ቀደም የነበሩ የማህበራዊ ፍትህ ችግሮችን የሚፈታ መሆኑን ጠቁመው፤ ለህዝቡ ፍትህን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ ሥራ እንደሚሰራም ጠቅሰዋል።
በእውነትና በህብረ ብሔራዊነት በመታገዝ ትግራይን ወደ እውነተኛ ብልጽግና ለማሸጋገር እንደሚሰራ መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!