ስፓርት

በሶማሊያ ከረጅም ዓመታት በኋላ ተመልካቾች የተገኙበት የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ

By Tibebu Kebede

December 28, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሶማሊያ ከረጅም ዓመታት በኋላ በርካታ ተመልካቾች የተገኙበት የእግር ኳስ ውድድር እያካሄደች ነው።

የሶማሊያ ክልሎች የእግር ኳስ ውድድር በሞቃዲሾ እየተካሄደ ይገኛል።

የሶማሊያ ክልሎችን የወከሉ የእግር ኳስ ቡድኖች እደረጉት በሚገኘው ጨዋታዎች በርካታ የሞቃዲሾ ከተማ ነዋሪዎች በስታዲየም ተገኝተዋል።

የአሁኑ ውድድር ለበርካታ ዓመታት በእርስ በእርስ ጦርነት እና በአልሸባብ የሽብር ጥቃት ስትታመስ ለቆየችው ሶማሊያ ትልቅ ድል መሆኑ ነው እየተነገረ የሚገኘው።

ይህ ውድድር ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ በተለየ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።

አሁን ላይ ውድድሩ ግማሽ ፍጻሜ ላይ ደርሷል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!