አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ግምታዊ ዋጋቸው 75 ሚሊየን 574 ሺህ 275 ብር የሆኑ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በተጠቀሰው ጊዜ ከተያዘው የኮንትሮባንድ እቃ ውስጥ ከሀገር ሊወጣ የነበረ 312 ኩንታል ቡና፣ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ አደንዛዥ እፆች፣ መድኃኒቶች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመዋቢያ ቁሳቁሶች፣ የመለዋወጫ እቃዎች፣ የተለያዩ አልባሳት እና የቀንድ ከብቶች ይገኙበታል፡፡
እቃዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩ 19 ተጠርጣሪ ግለሰቦችም በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት በፍተሻ፣ በብርበራ እና በተሽከርካሪ በመከታተል ሲሆን የጉምሩክ ሰራተኞች እና አመራሮች ከፌደራል እና ክልል ፖሊስ አባላት ጋር በቅንጅት በመስራት እነዚህን የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!