የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአራት መምህራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

By Tibebu Kebede

January 03, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአራት መምህራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው በሀገር ልማት ጥናት ኮሌጅ፣ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ በመምህርነት እና በተመራማሪነት ሲያገለግሉ ለቆዩት ምሁራን ነው የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጠው።

በዚህም መሰረት ዶክተር ጌታሁን አማረ፣ ዶክተር  በላይ ሰማኒ፣ ዶክተር ደገፍ ቶሎሳ እና ዶክተር ዋቅ ጋሪ ደሬሳ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።

የፕሮፌሰር ማዕረግ የተሰጣቸው መምህራን በተለያዩ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጆርናሎች የጥናትና የምርምር ስራ ማሳተማቸው ተጠቁሟል።

በሀይለዩሱስ መኮንን