አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊዮኔል ሜሲ ለባርሴሎና 644ኛ ጎሉን በማስቆጠር ለአንድ ክለብ ከፍተኛ ጎል በማስቆጠር በፔሌ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሻለ።
አርጄንቲናዊው አጥቂ ትናንት ምሽት ሪያል ቫያዶሊድ ከባርሴሎና ባደረጉት የስፔን ላሊጋ የባርሴሎናን ሶስተኛ ግብ በ65ኛው ደቂቃ ላይ በማስቆጠር የፔሌን ክብረ ወሰን ማሻሻል ችሏል።
ብራዚላዊው ኮኮብ ፔሌ ከፈረንጆቹ 1956 እስከ 1974 ድረስ ከሃገሩ ክለብ ሳንቶስ ጋር በነበረው ቆይታ 643 ግቦችን አስቆጥሮ ነበር።
ሊዮኔል ሜሲ ለባርሴሎና የመጀመሪያውን ግብ በፈረንጆቹ 2005 ያስቆጠረ ሲሆን ከክለቡ ጋር 10 የስፔን ላሊጋ እና አራት የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!