አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓኗ ካሳማ ከተማ ለጀግናው አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ ለሁለተኛ ጊዜ ተካሂዷል።
ውድድሩን ያስጀመሩት በጃፓን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አቶ ካሳ ተ/ብርሃን እና የማራቶን ሯጭ እና አሰልጣኝ ኮማንደር አበበ መኮንን መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በዚህ የ21 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ላይም ከ650 በላይ ተሳታፊዎች ተካፍለዋል።
የጃፓን የካሳማና ኢባራኪ ግዛት ከንቲቦችን ጨምሮበጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞችም በዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።
የውድድሩ መነሻና መድረሻ ቦታዎች በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተንቆጥቁጦ እንደነበር እና የኢትዮጵያ ባህላዊ ቡናም ለታዳሚያኑ መቅረቡን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!