አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ የ18 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ።
አንቶኖቭ 12 የተሰኘው የጦር አውሮፕላን በምዕራብ ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ ኤል ጀኔይና አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳ ከአምስት ደቂቃዎች በኋላ ነበር የተከሰከሰው።
በዚህም ሰባት የአውሮፕላኑን ሰራተኞች ጨምሮ ሦስት ዳኞች እና ስምንት መንገደኞች በአደጋው ሕይወታቸው ማለፉን የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ አመር መሀመድ አል ሃሰን ተናግረዋል፡፡
ከሟቾቹ መካከል አራቱ ህፃናት መሆናቸው ነው የተነገረው።
አውሮፕላኑ በቅርቡ በአካባቢው በተከሰተው የጎሳ ግጭት ሳቢያ ለተጎዱ ዜጎች እርዳታ ለማቅረብ ነበር ጉዞ የጀመረው።
በምዕራብ ዳርፉር ባለፈው እሁድ በተነሳ የጎሳ ግጭት እስካሁን 5ጨ48 ሰዎች መሞታቸው ይነገራል።
ምንጭ፡-ቢቢሲ