ስፓርት

ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በወንዶች የፊፋ የአመቱ ምርጥ ተጫዋችነት ሽልማትን አሸነፈ

By Tibebu Kebede

December 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖላንዳዊው አጥቂ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በወንዶች የፊፋ የአመቱ ምርጥ ተጫዋችነት ሽልማትን አሸነፈ፡፡

ሌዋንዶውስኪ ባለፈው የውድድር አመት ከክለቡ ባየርን ሙኒክ ጋር ስኬታማ የውድድር አመት ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

አጥቂው ከክለቡ ጋር የሶስት ዋንጫዎች ባለቤት ሲሆን፥ በ47 ጨዋታዎችም 55 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡

በጀርመን ቡንደስሊጋ እና በቻምፒየንስ ሊጉም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ጨርሷል፡፡

ሌዋንዶውስኪ አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲን እና ፖርቹጋላዊውን ክርስቲያኖ ሮናልዶን በመብለጥ የሽልማቱ አሸናፊ ሆኗል፡፡

በሴቶች የማንቼስተር ሲቲዋ ተከላካይ ሉሲ ብሮንዝ የሽልማቱ አሸናፊ ሆናለች፡፡

በአሰልጣኞች ደግሞ የሊቨርፑሉ የርገን ክሎፕ ሲያሸንፉ የባየርን ሙኒኩ ግብ ጠባቂ ማኑዌል ኑዌር በወንዶች የምርጥ ግብ ጠባቂነት ሽልማቱን አሸንፏል፡፡

የቶተንሃም ሆትስፐርሱ ሰን ሄዩንግ ሚን ባለፈው የውድድር አመት በርንሌይ ላይ ያስቆጠራት ጎል የፈረንጆቹ 2020 የፑሽካሽ ሽልማት አሸናፊ ሆናለች፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!