Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮ ሱዳን የባቡር ፕሮጀክት የመጀመሪያው የአዋጭነት ጥናት ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ ሱዳን የባቡር ፕሮጀክት የመጀመሪያው የአዋጭነት ጥናት በካናዳው የአማካሪ ተቋም ሲ ፒ ሲ ኤስ ትራንስኮም ቀረበ።

1 ሺህ 522 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውና አዲስ አበባን ከካርቱም የሚያገናኘው ይህ የባቡር ፕሮጀክት እንዲገነባ በሁለቱ ሀገራት መንግስታት ይሁኝታ ማግኘቱ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለኢትዮ ሱዳን የባቡር ፕሮጀክት የአዋጭነት ጥናት ለኢትዮጵያ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አፅድቆ ነበር።

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ኢኮሚኖያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታው የጎላ የባቡር መስመር ለመዘርጋት መሆኑን የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ገልፀዋል።

የባቡር ፕሮጀክቱ የሎጅስቲክ ፖሊሊ፣ የብሄራዊ የባቡር ኔትወርክ የኮንስትራክሽን ፍላጎት፣ ዓለም አቀፍ የባህር ትራንስፖርት መስመር እና ቀጣይነት ያለው ማህበራዊ እና ኢኮሚያዊ  እድገትን መሰረት ያደረገ መሆኑም ተነግሯል።

የሚገነባው የባቡር ፕሮጀክት ከካርቱም አልፎም በቀይ ባህር ላይ ከሚገኘው ፓርት ሱዳን ጋር እንደሚገናኝ ይጠበቃል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version