የሀገር ውስጥ ዜና

መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ ከሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት በቅርበት እየተከታተለ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

By Meseret Awoke

December 17, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ ከሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

“ችግሮችን ለመፍታት ሁልጊዜም ውይይትን የምንጠቀም በመሆኑ እንዲህ ያሉ ክስተቶች የሁለቱንም ሀገራት ትስስር አያላሉም” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፡፡

እንደ መልካም አጋጣሚ ወስደው በማራገብ ልዩነትን ለማስፋት የሚጥሩ አካላት የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ትስስር ያልተረዱ ናቸው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የሃገራቱን ታሪካዊ ግንኙነት ጥንካሬ በግልጽ አለመረዳት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!