አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013(ኤፍቢሲ) የወላይታ ቱሳ ስፖርት ክለብ መስራች አባ ጂኖ ቤናንቲ አረፉ።
ጣሊያናዊው አባ ጂኖ ቤናንቲ በጣሊያን ሀገር ሳን ሰቨሪኖ ደልማርክ በምትባል ምዕራብ ጣሊያን ከተማ እ.አ.አ. ሚያዝያ 23 ቀን 1944 ተወልደው በካቶሊክ ቤተ እምነት ሚሲዮናዊ ሆነው እ.አ.አ በወርሃ ሰኔ 1963 ዓ.ም የዛሬ 50 አመት ወደ ኢትዮጵያ በተለይም በወላይታ ማረፊያቸውን አድርገዋል።
አባ ጂኖ ቤናንቲ በዋናነት በካቶሊክ ቤተ እምነት መንፈሳዊ መምህር፣ በዱቦ ትምህርት ቤት የእንግሊዝኛ መምህርና ዳይሬክተር ሆነው ቆይተዋል።
በቀለም ትምህርትና በግብረ-ገብ እውቀት ትውልድን እየቀረፁ የቆዩና በስፋት በበጎ ተግባር ተሰማርተው ለብዙዎች መከታ ሆነዋል።
በሰፊው ህዝብ የሚታወቁት ግን በ1980ዎቹ በወላይታ አከባቢ ስመጥር በሆነው ወላይታ ቱሳ ስፖርት ክለብ መስራችነት ነበር።
በስፖርቱ ዘርፍ ታላቅ አሻራቸውን ያሳረፉት እኝህ አባት በተወለዱ 76 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
በመለሰ ታደለ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!