አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013(ኤፍቢሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮነን ከፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ ጋር ተወያዩ፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን ከፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡
በስልክ ባደረጉት ቆይታ በቅርቡ በጁንታው ላይ የተወሰደው የህግ ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን አስታውሰው በክልሉ እየተካሄደ ስለሚገኘው የሰብዓዊ ድጋፍም አስረድተዋል፡፡
እንዲሁም በጥፋት ኃይሉ ህወሓት የወደሙ መሰረተ ልማቶች ወደ አገልግሎት እንዲመለሱ መንግስት እያካሄደ ያለውን ጥረት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የጥፋት ኃይሉ ኤርትራውያን ስደተኞች በሚኖሩበት ካምፕ ዝርፊያ መፈጸሙን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት መንግስት ለስደተኞቹ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሚገኝም ነው አቶ ደመቀ ያብራሩት፡፡
በሌላ በኩል ሱዳን የሚገኙ ስደተኞችን ለመመለስ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ስደተኞች በሚመለሱበት ወቅት በወንጀል የተሳተፉ አካላትን የማጥራት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ነው የጠቀሱት፡፡
አቶ ደመቀ በመጨረሻም የአውሮፓ ህብረትም በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡
አቶ ደመቀ አክለውም ህብረቱ የጥፋት ኃይሉን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በሚዛናዊነት ለማየት መሞከር እንደሌለበት አሳውቀዋል፡፡
በስልክ ባደረጉት ውይይት በትግራይ ካለው ወቅታዊ ጉዳይ በተጨማሪ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የቀጠለውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይም አንስተው መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!