አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሻለ ሀሳባቸውን በምርጫ በማቅረብ ከዴሞክራሲ እሴቶች ካፈነገጡ አካሄዶች የታረመ ተግባር ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ የህግ ምሁራን ተናገሩ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የህግ ምሁራን የፖለቲካ ፓርቲዎች ከሽኩቻና ከማጣጣል አባዜ የወጣ ስልጡን የምርጫ ስልትን ሊተገብሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በምርጫ ተሳትፏቸው ለሙግት የሚያቀርቧቸው መከራከሪያዎች ለህዝቡ አማራጭ የሚሆን ጉዳይ መሆን ይኖርበታልም ነው ያሉት፡፡
የዘንድሮው ምርጫ ነጻ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ በቅድመ ምርጫ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠበቀው ቀዳሚ የቤት ስራም ይኸው መሆኑን አስረድተዋል።
በምርጫው የያዙትን አማራጭ ሀሳብ በማቅረብና ህዝቡን አሳምኖ መመረጥ ይቻላል ብሎ ጠንካራ የሀሳብ ዝግጅት ማድረጊያ ወቅት ስለመሆኑም ይናገራሉ።
አያይዘውም ካለፉት የኢትዮጵያ አፋኝና ፍትሃዊ ካልነበሩ የምርጫ ሂደቶች ትምህርትመውሰድ የግድ እንደሚሆንም ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጭምር የተሻለ የመወዳደሪያ ሜዳን በዴሞክራሲ መርሆዎች የከፈተ ነጻ ምርጫን የማካሄድ አቅም እንዳላት የምታሳይበት ሊሆን ይችላልም ነው ያሉት።
ለዚህም የምርጫው መሪ ተዋንያን የሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ሚናቸው ጉልህ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ምሁራኑ ለምርጫው አጠቃላይ ዴሞክራሲያዊነት እና የሂደቱ ስኬታማነት መንግስት ሰላምና ደህንነት ላይ ከወዲሁ መስራት እና አማራጭ ሀሳቦች ዝግጅት ላይ በጥልቀት እንዲሰራም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሀይለየሱስ መኮንን
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!