አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፡፡
ፕሬዚዳንቱ ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ በተደረገላቸው ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ይህን ተከትሎም ለሰባት ቀናት ራሳቸውን በማግለል ስራቸውን እየሰሩ ይቆያሉም ነው የተባለው፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም ከእርሳቸው ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች ተለይተዋልም ነው ያለው ፅህፈት ቤቱ፡፡
ፈረንሳይ በዚህ ሳምንት ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የምሽት ሰአት እላፊ መጣሏ ይታወሳል፡፡
በሃገሪቱ 2 ሚሊየን ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲኖርባቸው ከ59 ሺህ 400 በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት መዳረጋቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!