Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ በ200 ሚሊየን ብር ወጪ ከተማ የማስዋብ ስራ ሊከናወን ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ200 ሚሊየን ብር ወጪ የመንገድ ዳር አካፋዮችንና ፓርኮችን የማስዋብ ስራ ሊከናወን መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

በዚህ ስራ 28 ሺህ 162 ወጣቶች የስራ ዕድል እንደሚፈጠርላቸው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ገልጸዋል።

ከተማዋን የማስዋብ ተግባሩ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም የሚጀምር ሲሆን ስራውን የሚያከናውኑ ወጣቶች ልየታ ተካሂዷልም ብለዋል።

ወጣቶቹ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ስልጠና አግኝተው ወደ ስራ የሚሰማሩ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል 50 በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች ሴቶች እንደሆኑም ነው የተነገረው።

በአዲስ አበባ ከተማ በበጀት ዓመቱ ለ280 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር የታቀደ ሲሆን እስካሁን 148 ሺህ ለሚሆኑት የስራ ዕድል እንደተፈጠረ ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version