አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ለ28ኛ ጊዜ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 3 ሺህ 290 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው፡፡
የምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ተገኝተዋል፡፡
ዶክት ሙሉ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ኮሮና ቫይረስ በመከሰቱ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የከፍተኛ ትምህርት አንዱ ፈተና እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
በሌላ በኩል በትግራይ ክልል የተፈጠረው የጸጥታ ሁኔታ መደፍረስ ለተማሪዎች ሁለተኛ ፈተና እንደነበርም ነው የጠቀሱት፡፡
ተማሪዎች እነዚህን ፈተናዎች ተቋቁመው ለስኬት በመብቃታቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
በተለይም ዩኒቨርሲቲው እና የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ከወላጆች የተቀበሉትን አደራ ጠብቀው ተማሪዎቹን ለዚህ ዕለት ስላበቋቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የመጀመሪያ ትውልድ የሆነው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ 383 የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ሲኖሩት ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል፡፡
68 በመቶ የሚሆነው የዩኒቨርሲቲው ትምህርት የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሲሆኑ በዛሬው ዕለት ከተመረቁት ተማሪዎች መካከል ደግሞ 30 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው፡፡
በምስክር ስናፍቅ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!