የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ አትክልት ተራ በሃይሌ ጋርመንት ገበያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

By Meseret Awoke

December 17, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ አትክልት ገበያ ማዕከል በሃይሌ ጋርመንት አካባቢ አዲስ በተገነባው የገበያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

አዲሱ የገበያ ማዕከል የቀድሞውን የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫን በመተካት የሚሰራ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ጃንሜዳ በጊዜያዊነት የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ሆኖ ሲያገለግል መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ስፍራው ከ500 በላይ ለሚሆኑ ነጋዴዎች መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ገልጸዋል፡፡

የንግድ ሼዶቹ በአብዛኛው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ ሲሆን ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ አለመጠናቀቁ ነው የተነገረው፡፡

ሆኖም ግንባታቸውን በቅርቡ የማጠናቀቅ ስራው ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዱሬቲ ቶሎሳ