አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የካናዳ አነስተኛ ንግድ፣ የወጪ ንግድ ማስተዋወቂያ እና ዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ሜሪ ኒግ በኢትዮጵያ፣ በደቡብ አፍሪካና ኬኒያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ።
የሚኒስትሯ ጉብኝት የአፍሪካና ካናዳን የንግድ ዘርፍ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ሚኒስትሯ ከታህሳስ 26 እስከ ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም በሚኖራቸው በቆይታ ከንግድ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ካናዳ አዳዲስ የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር ከአፍሪካ ጋር በትብብር እንደምትሰራ ተጠቅሷል፡፡
ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ የካናዳ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን፣ ሥራ ፈጣሪዎችና አምራቾችን በኢትዮጵያ ካሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ይወያያሉ ተብሏል።
የሚኒስትሯ ጉብኝት በአፍሪካ ሃገራት እና በካናዳ መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እና ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሸጋር እንደሚያስችል በኢትዮጵያ ከካናዳ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!