አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምስራቅ አፍሪካዊቷ ኬንያ በቀጣዩ ወር የኮሮና ቫይረስ ክትባትን እንደምትቀበል ገለጸች፡፡
የጤና ሚኒስትሩ ሙታሂ ካግዌ 24 ሚሊየን መጠን የያዘ ክትባት ማዘዛቸውን ነው የገለጹት፡፡
የጤና ሚኒስትሩ በመጀመሪያው ዙር በወረርሽኙ ተጋላጭ የሆነ ዜጎች እንደሚሰጥ ነው ያስታወቁት፡፡
የጤና ሚኒስትሩ ኬንያ የምትቀበለው የኮሮናቫይረስ ክትባት ኦክሶፎርድ ዩኒቨርስቲ ያበለጸገውን አስትራዜኔካ የተሰኘውን ነው ብለዋል፡፡
በመጀመሪያው ዙር 20 በመቶ ለሚሆነው የሀገሪቱ ህዝብ ክትባት እንደሚዳረስ የገለጹት የጤና ሚኒስትሩ የኦክስፎርዱ ክትባት ከሌሎቹ አንጻር ርካሽ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የአሁኑ 24 ሚሊየን መጠን ያለው ክትባት ኮቫክስ ከተሰኘው ከዓለም አቀፉ የክትባት ጥምረት በነጻ የተገኘ ነው ብለዋል፡፡
ሆኖም ተጨማሪ 10 በመቶ ዜጎቿ ክትባት እንዲወስዱ 10 ቢሊየን ሽልንግ መበጀታቸውንም ገልጸዋል፡፡
ኮቫክስ አፍሪካና ደቡብ አሜሪካን ጨምሮ እስከ 2021 መጨረሻ ድረስ 20 ቢሊየን መጠን ያለው የኮሮና ቫይረስ ክትባት በዓለም ዙሪያ ለማዳረስ ማቀዱ ተሰምቷል፡፡
ምንጭ፡-ኔሽን
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!