የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ ከፖርቹጋል አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Abrham Fekede

December 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ከሆኑት ሄሌና ማልካታ ጋር በሀገራቱ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተገለጸ፡፡

በውይይቱ ላይ ፖርቹጋል ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ጥንታዊ እና ታሪካዊ ቁርኝት መነሳቱ ነው የተጠቀሰው፡፡

ዶክተር ሂሩት በተለይም ኢትዮጵያ ድጋፍ ባስፈለጋት ጊዜ ከጎኗ የቆመች ወዳጅ ሀገር መሆኗን አንስተዋል፡፡

እንዲሁም ኢትዮጵያ ከየትኛውም የአውሮፓ ሀገር በፊት ከፖርቹጋል ጋር የመንግስት ለመንግስት ግንኙነት እንደነበራትም አስታውሰዋል፡፡

ሚኒስትሯ በውይይቱ ላይ የአሁኑ ትውልድ ይህንን ታሪካዊ ወዳጅነት አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

አምባሳደር ሄሌና በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ መስራት የሚያስችሉ በርካታ ዘርፎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

በቱሪዝም ልማት፣ ዕደ ጥበባት በማጎልበት፣ በስፖርት ልማት፣ በሙዚየም ማደራጀት፣ በባህላዊ መስህቦችና ተያያዥ መስኮች መስራት እንደሚቻል አብራርተዋል፡፡

በቀጣይም ዘርፎቹ በባለሙያ ተጠንተውና ተለይተው የጋራ መግባቢያ ሰነድ እንደሚፈረም መግባባት ላይ መደረሱን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!