Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኳታራዊው ባለሃብት ለህዳሴ ግድብ የ100 ሺህ ዶላር ቦንድ በድጋሚ ገዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኳታራዊው ባላሀብት አብደላ ሳሌም ሱሌይቲን ኢትዮጵያ በሚገኘው ድርጅታቸው አማካኝነት የ100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ቦንድ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ገዙ።
ባለሀብቱ የአል ሱሌይቲን ግሩፕ ኩባንያ ባለቤት እና ሊቀ መንበር ናቸው።
ባለሀብቱ ከዚህ ቀደም በ2007 ዓ.ም ተመሳሳይ መጠን ያለው የሕዳሴ ግድብ ቦንድ በመግዛት ድጋፋቸውን መግለጻቸውን በዶሃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
የገዙት ቦንድ የመመለሻ ጊዜው የደረሰ በመሆኑ በዚሁ ገንዘብ በድጋሚ የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል።
ቀሪው የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት እንዲጠናቀቅ’ መልካም ምኞታቸውን የገለጹት ባለሀብቱ “ግድቡ ለኢትዮጵያ እና ለታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል” የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል።
በኳታር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ በበኩላቸው አብደላ ሳሌም አል ሱሌይቲን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እያሳዩ ያለው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦም በኢትዮጵያ መንግስት እና ሕዝብ ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የባለሃብቱ ተወካይም በኤምባሲው ተገኝተው የቦንድ ሰርተፊኬቱን ከአምባሳደር ሳሚያ ተቀብለዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version